በዘንድሮ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ከ54ቱ አባል ሀገሮች 39ኙ ሞሮኮ ተመለሳ ሕብረቱን እንድትቀላቀል ድጋፍ በመስጠታቸው አሸናፊው "አንድነት" ሆኗል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ሞሮኮ ከአህጉራዊው ድርጅት ለሰላሳ ዓመታት በላይ ተለይታ ከቆየች በኋላ እንደገና መመለሷን የአፍሪካ ኅብረት በደስታ ተቀብሎታል። ሀገሪቱ እ.አ.አ በ 1984 ዓ.ም ከኅብረቱ እንድትወጣ ያደረጋት ዓብይ ምክንያት መፍትሄ ካላገኘ ግን ሽግግሩ የተሳካ ላይሆን ይችላል። አኒታ ፓወል ከአዲስ አበባ ያደረሰችን ዘገበ አለ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋለች።