በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ከግንቦት ሰባት ጋራ በመተባበር የሽብር ወንጀል ክስ ቀርቦበት ጉዳዩን በመከታተል ላይ የሚገኘው አቶ አስቻለው ደሴ በድብደባ የተጎዳውን የዘር ፍሬ እንዳይታከም እክል እንደገጠመው በዛሬው ዕለት ለፍርድ ቤት ማመልከቱ ተሰማ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ጠበቃው አቶ አለልኝ ምሕረቱ የዛሬው የችሎት ሁኔታ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም ተከሳሹ የተጎዳውን አካሉን ለፍርድ ቤቱ ገልጦ በማሳየቱና በዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል በመጎብኘቱ ክትትል ተጀመሮለት እንደነበር መናገሩን ገልፀው ነገር ግን በሂደት ለተገኘው ቅዱስጳውሎስ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ቀጠሮ ሳይወሰድ እንደቀረ ተናግሯል ብለዋል።
ጽዮን ግርማ ጠበቃውን አቶ አለልኝ ምሕረቱን አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች።
Your browser doesn’t support HTML5
አቶ አስቻለው ደሴ በድብደባ የተጎዳ አካሉን ለመታከም እክል እንደገጠመው ለፍርድ ቤት አመለከተ