በሱስ የተጠቁ ወጣቶችን ለማዳን ተጠቃሽ ሚና ያላቸው ማገገሚያ ተቋማት

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ በሱስ እና ተያያዥ ችግሮች የሚጠቁ ወጣቶች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ቢኾንም ከሱስ ለማገገም የሚረዱ ተቋማት ግን በስፋት አለመኖራቸውን ባለሞያዎች ይገልጻሉ። ይኹን እንጂ በቅዱስ ጳውሎስ ሜዲካል ኮሌጅ ሥር የሚገኘው የሱስ ማገገሚያ ማዕከል፣ ለበርካታ ወጣቶች ድጋፍ በማድረግ ወደ መደበኛ ሕይወታቸው እንዲመለሱ እየረዳ ይገኛል። በተቋሙ ውስጥ ከነበረበት ሱስ ለማገገም መቻሉን ለአሜሪካ ድምፅ የተናገረ አንድ ወጣትም፣ ለሌሎች ወጣቶች ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።