በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የቆቦ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደርቤ በለጠ ትላንት ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን በአካባቢው ነበርን ያሉ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።
Your browser doesn’t support HTML5
የቆቦ ከተማ የብልጽግና ጽ/ቤት ሓላፊ በታጣቂዎች መገደላቸውን የአካባቢው ሰዎች ገለጹ
በአካባቢው ላይ በጥርስ መፋቂያ ንግድ ላይ ተሰማርቶ የነበረ አንድ ወጣት በወቅቱ በደረሰብ ጉዳት ምክኒያት ዛሬ ሕይወቱ ማለፉን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ፣ በአቶ ደርቤ መገደል ማዘናቸውን በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።
ለግድያው እስካኹን በይፋ ሓላፊነት የወሰደ አካል የለም።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ይከታተሉ፡፡