ከበርበራ ጋር ለተያያዙ መልዕክቶች ሬድዋን መልስ ሰጡ

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ በደረሱበት የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ላይ እየተሰጡ ያሉ መግለጫዎችና አስተያየቶች “ያልጠበቅናቸው አይደሉም” ሲሉ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትሩ ሬድዋን ሁሴን ዛሬ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።

መግለጫዎቹን በተለያየ መልክ እንደሚመለከቱ የጠቀሱት አምባሳደር ሬድዋን “በመጀመሪያ ደረጃ ኢትዮጵያ በልማቷ ከቀጠለችና ከዓለም አቀፍ መድረክ ጋር የሚያገናኛትን የባሕር በር ካገኘች በሁለት እግሯ ልትቆም ትችላለች የሚል ሥጋት አላቸው” ያሏቸው አካላት “እሳትና ነዳጅ ሲያቀብሉ አይተናል” ብለዋል።