በሩሲያ የዩክሬን ጦርነት እውነታዎችን የሚያዘክር የጥበባት ዐውደ ርእይ በኮፐንሃገን ቀረበ

Your browser doesn’t support HTML5

በዴንማርክ ዋና ከተማ ኮፐንሃገን፣ የዩክሬን ባህል ማዕከል በኾነ ቤት ውስጥ፣ “በጀግንነት መመስከር - የዩክሬን ጦርነት ማስታወሻዎች” የሚል ርእስ የተሰጣቸው ጥበባዊ ሥራዎች፣ ለእይታ ቀረቡ፡፡ በዐውደ ርእዩ፣ በከባድ ፍርሃት የተዋጡ ዘመዶቻቸውን ያጡ ሕፃናት ይታያሉ፡፡ በሩሲያው የዩክሬን ደም አፋሳሽ ጦርነት፣ ብዙም ትኩረት ያልተሰጣቸው፣ የግል ሕይወት ገጠመኞች፥ ዐዲስ በተዘጋጀው የሥዕል ዐውደ ርእይ ግድግዳ ላይ ለእይታ ቀርበርዋል፡፡