በካማሺና መተከል ሰላም መስፈኑን ነዋሪዎች ገለፁ
Your browser doesn’t support HTML5
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም በመስፈኑ ያለስጋት መንቀሳቀስ መቻላቸውንና ተቋርጦ የነበረው ማኅበራዊ መስተጋብር መጀመሩን አንዳንድ የካማሺና መተከል ዞን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ሀሩን ኡመር ታጣቂዎች ከክልሉ መንግሥት ጋራ የሰላም ስምምነት ተፈራርመው ከገቡ በኋላ ሰላም መስፈኑን ተናግረዋል።የጉህዴን ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ በበኩሉ ሰላም መስፈኑ የልማት ሥራዎችን ለመሥራት እገዛ እንዳደረገ ገልፀዋል።