አፍሪካ የውድድር ሳይሆን የትብብር ሜዳ መሆን አለባት ሲሉ አዲሱ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

አፍሪካ የውድድር ሳይሆን የትብብር ሜዳ መሆን አለባት ሲሉ አዲሱ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ

በሁለተኛ ቀን የኢትዮጵያ ቆይታቸው ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጋራ የተወያዩት አዲሱ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ፣ በሀገራቸው ድጋፍ የተገነባውን የአፍሪካ በሽታዎች መቆጣጠርና መከላከል ማዕከልም መርቀው ከፍተዋል።

በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር አፍሪካ ሀያላን ሀገሮች የሚተባበሩባት እንጂ ውድድር የሚያደርጉባት ሜዳ መሆን የለባትም ያሉት ሚኒስትሩ፣ አሕጉሪቱ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት እንደሚገባም ገልፀዋል።

/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/