ታውከው የነበሩ ትምህርት ቤቶች ተከፈቱ

Your browser doesn’t support HTML5

ታውከው የነበሩ ትምህርት ቤቶች ተከፈቱ

ሁከት ተከስቶባቸው የነበሩ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቤቶች መከፈታቸውን የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዛሬ ገልጿል።

ከኦሮምያ ክልላዊ ሰንደቅ ዓላማና መዝሙር ጋር በተያያዘ ሰሞኑን አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተፈጥረው በነበሩ ሁከቶች በሰውና በንብረት ላይ ጉዳቶች መድረሳቸው ተዘግቧል።

የሃገሪቱ ዋና እንባ ጠባቂ ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ፣ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ፀሃፊ የሆኑት የኢሶዴፓ ምክትል ፕሬዚደንት ዶ/ር ራሄል ባፌ ለችግሩ መከሰት መንግሥትን ተጠያቂ አድርገዋል።

መንግሥት በበኩሉ ችግሩን የፈጠሩት ‘ሁከት እንዲነግሥ የሚፈልጉ የተደራጁ አካላት ናቸው’ ይላል።

/ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/