የዓለም ዋንጫ ክስተቶች

Your browser doesn’t support HTML5

ከእስካሁኖቹ የዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታዎች ልብ አንጠልጣይ እንደሆነ የተነገረለትን ጨዋታ በማሸነፍ አርጄንቲና 3ኛ የዓለም ዋንጫዋን አንስታለች።የእግር ኳሱ ዓለም ሊቸረው የሚችለውን ሁሉ ድል ያሳካው ሜሲ፣ የዓለም ክስተት መሆኑን አስመስክሯል ከካታር ንጉስ ሼህ ታሚም ቢን ሀማድ አልታኒ የተበረከተለትን “ቢሽት” የተባለ ብዙውን ጊዜ ከንጉሣዊ ቤተሰብ ጋር የተቆራኘና በልዩ አጋጣሚዎች የሚለበስ የክብር ካባ ደርቦ፣ ዋንጫውን ከቡድኑ አባላት ጋር ወደ ላይ ከፍ አድርጓል፡፡