የኢትዮጵያዊያኑ አባት እና ልጅ ትኩረትን የሳበ የዓለም ዋንጫ ጉዞ

Your browser doesn’t support HTML5

ለኢትዮጵያ የስፖርት ቤተሰብ ስሙ አዲስ ያልሆነው ቴዎድሮስ ባጫ እና ልጁ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ሁሉንም የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች እንዲታደሙ በፊፋ ከተጋበዙ ሰነባብተዋል። ካታር ላይ ከዓለም ዕውቅ የስፖርት ሰዎች ጋር በሚገናኙባቸው ቅጽበቶች የሀገራቸውን ባህል በማስተዋውቅ ጭምር የሚያሳልፉት አባት እና ልጅ "የእግር ኳስ ፍቅር " ብሎም እዚህ ለመድረስ ያለፉበት መንገድ የብዙዎችን ትኩረት የሚስብ ነው ። ልዩ የዓለም ዋንጫ ሽፋናችን እንግዶች አድርገናቸዋል ።