የተሰናባቹ 2014 ግምገማ እና የአዲሱ ዓመት ምኞት - ከነዋሪዎች አንደበት

ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ

እየተገባደደ ያለው የ2014 ዓ/ም በተለይ ከሠላምና ጸጥታ ጉዳዮች አንጻር አስቸጋሪ እንደነበር የገለፁት የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ኢትዮጵያዊያን ዕሁድ የሚጀምረው አዲስ ዓመት የተሻለ እንደሚሆን ተስፋቸውን ገልጸዋል።

አዲሱ የ2015 ዓ/ም የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ሰላማዊ እልባት የሚያገኝበት እንዲሆን ምኞታቸውን ያንጸባረቁም አሉ።

ሌሎች ደግሞ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ቢሆን ተሳኩ ያሏቸውን የሕዳሴውን ግድብ ሙሌት የመሳሰሉ ክንውኖች በአዎንታዊነት ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያዊያን አዲሱን የ2015 ዓ/ም ለመቀበል እየተዘጋጁ ባሉበት በዚህ ሳምንት የአሮጌውን የ2014 ግምገማቸውን እና ለ2015 ያላቸውን ምኞታቸውን መጠየቃችንን ቀጥለናል።

የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን አስተያየት ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የተሰናባቹ 2014 ግምገማ እና የአዲሱ ዓመት ምኞት - ከነዋሪዎች አንደበት