የአውሮፓ ኅብረት የሰብዓዊ መብቶች ልዩ ተወካይ የኢዮጵያ ቆይታ

Your browser doesn’t support HTML5

የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ማነቆዎችን መቅረፍ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር መወያየታቸውን የአውሮፓ ኅብረት የሰብዓዊ መብቶች ልዩ ተወካይ ገለጹ።ልዩ ተወካዩ ኤሞን ጊልሞር በኢትዮጵያ ያደረጉትን የሦስት ቀናት ጉብኝት ሲያጠናቅቁ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ከሰብዓዊ ድጋፍ ጉዳይ በተጨማሪ በሰብዓዊ መብቶች እና በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እየተወሰዱ ባሉ እርምጃዎች ዙሪያም ከተለያዩ አካላት ጋር እንደተወያዩ አብራርተዋል።