ስለምጡቁ የጄምስ ዌብ ቴሌስኮፕ፦ ቆይታ ከዶ/ር ብሩክ ላቀው ጋር

.

ለዘመናት የሰው ልጅ መልስ ለማግኘት ካወጣ ከወረደባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ፣ የምንኖርባት ዓለም በዛሬ ቅርጽ እና ይዘቷ ላይ እንዴት ደረሰች ? የሚለው ነው። ለዚህ ጥያቄ መልስ ለማግኘት ዓመታትን የተሻገሩ ምርምሮች፣ የጠፈር አሰሳዎች እና ዘርፈ ብዙ ርብርቦች ተካሄደዋል ።

ዩናይትድ ስቴትስ ከሰሞኑ በጠፍር ምርምር ዘርፍ ከተሰሩት ሁሉ በእጅጉ ዘመናዊ የሆነውን የጄምስ ዌብ ቴሌስኮፕ ከሰሞኑ ወደ ጠፈር ልካለች ። ቴሌስኮፑ በህዋ ላይ በሚያደርገው ጉዞ ለሰነበተቱት በርካታ የሰው ልጆች ጥያቄዎች መልስ በማስገኘት ረገድ ያለቀ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል ።

ስለ ግዙፉ ቴሌስኮፕ እና ፋይዳው የበለጠ ለማወቅ ሀብታሙ ስዩም ከ30 ዓመታት በላይ በዩናይትድ ስቴትስ የጠፈር ምርምር ተቋም ውስጥ ያገለገሉትን፣ በቅርቡ ጡሮታ ከወጡ በኃላም በተለያየ የስራ ኃላፊነት ዕውቀታቸውን እና ልምዳቸውን በማበርከት ላይ የሚገኙትን ዶ/ር ብሩክ ላቀውን በስልክ አግኝቷቸዋል።

ሙሉ መሰናዶውን ያዳምጡ ፦

Your browser doesn’t support HTML5

ስለ ምጡቁ የጄምስ ዌብ ቴሌስኮፕ ፦ አጭር ቆይታ ከዶ/ር ብሩክ ላቀው ጋር