ኢትዮጵያን ዳግም ወደ አጎአ ተጠቃሚነት ለመመለስ ስለ ተደረገ ጥረት

.

ዩናይትድ ስቴትስ ደርሰዋል ያለቻቸው የሰብዓዊ መብት ረገጣዎችን ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ የንግድ ዕድል ተጠቃሚነት አባልነት ሰርዛለች ። በፕሬዚደንት ባይደን የተፈረመው ውሳኔ ከነገው ዕለት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ይጠበቃል ።

የአሜሪካ ኢትዮጵያ የህዝብ ግኑኝነት ኮሚቴ የተባለው ተቋም ፣ ውሳኔው የብዙ ኢትዮጵያዊያንን የስራ ዕድል የሚዘጋ ፣ በሁለቱ ሀገራት የንግድ መጠቃቀም ላይ ጉዳት የሚያደርስ ነው በሚል ሲቃወም ቆይቷል።

በዋዜማው ሀብታሙ ስዩም ለኮሚቴው ሊቀመንበር አቶ መስፍን ተገኑ ደውሎላቸዋል ። ። በመጨረሻዎቹ ቀናት እያደረጉት ስላለው ጥረት እና የቀጣይ ጊዜ ዕቅዳቸው አስረድተውናል ።

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያን ወደ አጎአ ተጠቃሚነት ዳግም ለመመለስ ስለተደረገው እንቅስቃሴ