አዲስ አበባ —
በኢትዮጵያ መንግሥት የተቋቋመው የሚኒስትሮች ግብረ ኃይል፣ የኢሰመኮና የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽ/ቤት ምክረ ሐሳቦችን ተግባራዊ የማድረግ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ።
በምክረ ሐሳቡ መሰረት መንግሥት ወደ ተግባር መግባቱን “ትክክለኛ እርምጃ” ሲሉ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ አድንቀዋል፡፡ ኮሚሽኑ ለግብረ ኃይሉ የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርግና ሥራውን ከሰብዓዊ መብት አንጻር እንደሚከታተልም ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡
የሚኒስትሮች ግብረ ኃይል ያዘጋጀው ስትራቴጂና የድርጊት መርኃ ግብር፣ በምክረ ሐሳብ ከቀረቡት አካባቢዎች በተጨማሪ፣ በግጭቱ ምክንያት የተፈጸሙ ሁሉንም ከባድ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንደሚሸፍን ያብራሩት ደግሞ የፍትህ ሚኒስቴር የፕሬስ ሴክሬቴሪያት ኃላፊው አቶ አወል ሱልጣን ናቸው፡፡
/ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/