አዲስ አበባ —
የተባበሩት መንግሥታት የህወሓትን ድርጊት በማውገዝ ድምጹን እንዲያሰማ ኢትዮጵያ ማሳሰቧን አስታወቀች።
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ ምክትል ዋና ጸሃፊ ሮዝመሪ ዲካርሎ፣ ድርጅቱ ኢትዮጵያ ካሉባት ፈተናዎች እንድትወጣ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ስለመሆኑ መግለጻቸውን አንስተዋል፡፡
አሁን ላይ የመንግሥት ዋነኛ ትኩረቶች ከህወሓት ጋር የተያያዘው የሰሜን ኢትዮጵያ ጉዳይ እና ከሱዳን ጋር ያለው የድንበር ውዝግብ መሆናቸውንም ነው ቃል አቀባዩ የተናገሩት፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
ኢትዮጵያ ህወሓት እየፈጸመ ነው ላለችው ተመድ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀች