Your browser doesn’t support HTML5
ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያን ጨምሮ በስድስት ሃገራት የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል አለች
የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስተር አንተኒ ብሊንከን ሰኞ ዕለት ዓመታዊ የዘር ማጥፋት እና የጭካኔ መከላከል ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱም ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞባቸዋል የተባሉ ስድስት ተጠቅሰዋል፡፡ ሃገራቱም በርማ በመባል የምትታወቀው ማይናማር፣ ቻይና፣ ኢትዮጵያ ፣ ኢራቅ ሶሪያ እና ደቡብ ሱዳን ናቸው፡፡
ሚኒስተሩ በተጨማሪም ለውጥ ለማምጣት "በዲፕሎማሲ፣ በውጪ ሃገር እርዳታ፣ እውነታውን በማፈላለግ ተልዕኮ፣ በገንዘብ፣ በተሳትፎ ድጋፍ እና ይህን በመስሉ እጃቸን ላይ ባሉ የተቀናጀ ዓለም አቀፍ ተጽእኖ እና ምላሽ መስጠት የሚረዱ ሪፖርቶችን በማውጣትም ባለው ነገር ሁሉ እንጥራለን" ብለዋል፡፡