“ይማሩ”-ማህበራዊ መገናኛን ለትምህርት ያዋለው አምድ

Your browser doesn’t support HTML5

“ ይማሩ ” በመላ ዓለም ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የእንግሊዝኛ ክህሎትን የሚያስተምር የዮቲዩብ አምድ (ቻናል ) ነው። ከ160ሺ በላይ ተከታዮች ያሉት አምዱ ፣ ወደ 90 የሚጠጉ በጥሩ ጥራት የተቀናበሩ ማስተማሪያ ምስሎችን አካቷል። በወጣቶች የተመሰረው “ይማሩ” ቀለል ባለ አቀራረብ የእንግሊዝኛ ንግግርን ለማሻሻል ይረዳሉ ያላቸውን ሀሳቦች በማቀበል ላይ ይገኛል።