በኢትዮጵያዊያን ስለተዘጋጀው የአፍን አፍንጫ መሸፈኛ ፋሽን ትርኢት

ዲኬቲ ባዘጋጀው የበይነ-መረብ ላይ የፋሽን ትርኢት ላይ ከታዩ የፊት እና አፍንጫ መሸፈኛዎች በጥቂቱ

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ በቤተሰብ ዕቅድ እና በስነ-ተዋልዶ ጤና ላይ ለዓመታት በሰራቸው ስራዎች የሚታወቀው ዲኬቲ ኢትዮጵያ ለየት ያለ የበይነ -መረብ ላይ ትርኢት እያሳየ ይገኛል።

ትርኢቱ ደግሞ በዕውቅ የፋሽን ንድፍ ባለሙያዎች የተዘጋጁ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛዎች የሚታዩበት ነው።

ሀብታሙ ስዩም ያናገራቸው የድርጅቱ የገበያ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ እመቤት አቡ የትርኢቱ ዓላማ ወጣቶች ጤናቸውን እየጠበቁ ሊደምቁባቸው ከሚችሉባቸው መላዎች ጋር ማስተዋወቅ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ሙሉ ቃለ-ምልልሱን ያዳምጡ፦

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያዊያን ስለተዘጋጀው የፊት እና አፍንጫ መሸፈኛ ፋሽን ትርኢት