ፌደራል መንግሥቱ ለጌዴኦ ቀውስ ግልፅና ዘላቂ መፍትኄ እንዲሰጥ የጌዴዖ ምሁራን ማኅበር ጠይቋል።
በሕዝቡ ላይ ለደረሰው ከፍተኛ ጉዳት ተመጣጣኝ ትኩረት በክልልና በፌደራል መንግሥት ባለመሰጠቱ ችግሩ የከፋ መሆኑን በመግለፅ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የመከሩት ምሁራን መንግሥትን በምክንያትነት ከስሰዋል።
ደቡብ ክልል —
ሲቪሎችን የገደሉ፣ ያፈናቀሉና ንብረት ያወደሙ ግለሰቦችን መንግሥት ይዞ ሕግ ፊት እንዲያቀርብም ጠይቀዋል።
በሺሆች የሚቆጠሩ የጌዴዖ ብሔረሰብ አባላት አሁንም ችግር ላይ እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን ለ364 ሺህ ሰው ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ የጌዴዖ ዞን አስተዳዳሪ አሳስበዋል።
የብሄራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ተፈናቃዮችን ከበልግ እርሻ ወቅት በፊት ወደየቀያቸው ለመመለስ የሚያስችል ጥረት እያደረገ መሆኑንና ዲላ ከተማ ላይም ማዕከል ማቋቋሙን ገልጿል።
(ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።)
Your browser doesn’t support HTML5
ለጌዴዖ ዘላቂ መፍትኄ ተጠየቀ