በአማራና በኦሮሚያ- የተከሰተው አድማ
Your browser doesn’t support HTML5
በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የንግድ ቤቶችና የሕዝብ ትራንስፖርት ተቋማት አገልግሎት ማቋረጣቸውን ነዋሪዎች እየገለፁ ነው። ለዚህም በምክንያትነት የሚያስቀምጡት በባሕርዳር ከተማ የዛሬ ዓመት በተቃውሞ ወቅት በፀጥታ አካላት የተገደሉ ወጣቶችን ለማስታወስና አሁን በአማራ ክልል ተግባራዊ መደረግ የጀመረውን የቀን ገቢ ግምት በመቃወም ነው። በኦሮሚያ ደግሞ የታሰሩ የፖሊተካ አመራሮች ይፈቱ የሚል እና በቀን ገቢ ግምቱ ላይ መፍትሔ አልተሰጠንም የሚል ይገኝበታል።