በጎንደር ንብረት ሊያቃጥሉ ነበር የተባሉ በቁጥጥር ስር መሆናቸውን የክልሉ መንግስት አስታውቋል
Your browser doesn’t support HTML5
በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ ትናንትና እና ከትናንት በስቲያ ከቃጠሎ የተረፈውን የገበያ ቦታ እና ሌሎች ንብረቶችን ሊያቃጥሉ ነበር ያሏቸውን ግለሰቦች መያዛቸውንና ለፖሊስ ማስረከባቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ። በጎንደር ተጨማሪ የቃጠሎ አደጋ ይደርሳል የሚል ስጋት እንዳላቸውም ገልጸዋል።