ሴቶች ከቡናዉ እንዱስትሪ የሚያገኙት ጥቅም እጅግ አናሳ ነዉ

Your browser doesn’t support HTML5

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን March 8 ወይም የካቲት 29 በሚከበርበት አጋጣሚ አራተኛዉ ዓለም አቀፍ የቡና ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሂዶ ነበር ። ጉባኤዉ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝና የአፍሪቃ ልማት ባንክ ልዩ መልክተኛ ጄራልዲን ፌሬዜር ሞልጌቲ ሴቶች ከወንዶች ሲነጻጸር ከቡናዉ ኢንዱስቲሪ የሚያገኙት ጥቅም እጅግ አናሳና ኢ-ፍትሃዊ መሆኑን አስምረዉበታል።