በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“እሳቱ ከርቀት እየታየኝ ነው ቤቴን የለቀኩት” - የሳንታ ሞኒካ ከተማ ነዋሪ


“እሳቱ ከርቀት እየታየኝ ነው ቤቴን የለቀኩት” - የሳንታ ሞኒካ ከተማ ነዋሪ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:53 0:00

“እሳቱ ከርቀት እየታየኝ ነው ቤቴን የለቀኩት” - የሳንታ ሞኒካ ከተማ ነዋሪ

በደቡባዊ ካሊፎርኒያ ግዛት የቀጠለው ሰደድ እሳት፣ እስከ አኹን የ24 ሰዎችን ሕይወት ሲቀጥፍ፣ 12 ሺሕ የሚደርሱ ቤቶችን አውድሟል። ከሟቾቹ መካከል ስምንቱ በፓሲፊክ ፓላሳዴስ አካባቢ በተዛመተው እሳት የሞቱ መሆናቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ሰደድ እሳቱን ለማጥፋት የእሳት አደጋ ሠራተኞች ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ባሉበት በዚህ ወቅት፣ እንደ ዐዲስ ሊነሳ ይችላል ተብሎ የተሰጋው ጠንካራና ደረቅ ንፋስ እሳቱን ሊያባብሰው እና ከቁጥጥር ውጪ ሊያደርገው ይችላል ሲሉ የትንበያ ባለሞያዎች አስጠንቅቀዋል።

የአሜሪካ ብሔራዊ የአየር ትንበያ አገልግሎት በአወጣው ማስጠንቀቂያ፣ ዛሬ ማክሰኞ ሊጨምር ይችላል ተብሎ የተሰጋው ጠንካራ ንፋስ በሰዓት እስከ 100 ኪሎሜትር ሊጓዝ ይችላል እንደሚችል ተነግሯል።

እስከ ትላንት ሰኞ ምሽት ድረስ 100 ሺሕ ሰዎች ከአካባቢያቸው ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው ሲሆን፣ አዲስ ንፋስ ሊነሳ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ መውጣቱን ተከትሎ ነዋሪዎቹ ወደ መኖሪያቸው መመለስ እንደማችሉ ተመልክቷል።

እስካሁን በተደረጉ ቅድመ ጥናቶች መሠረት፣ እሳቱ በንብረት ላይ ያደረሰው ጉዳት እና የኢኮኖሚ ኪሳራ ከ130 እስከ 150 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።

ሰኞ ታኅሣሥ 29 ቀን 2017 ዓ.ም በካሊፎርኒያ ግዛት በፓስፊክ ፓላሴድስ የተነሳውና አዋሳኝ በኾኑ ሌሎች ከተሞች የተዛመተው ሰደድ እሳት ፓስፊክ ፋየር ወይም የፓስፊክ እሳት የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

ውድመት ከደረሰባቸው ከተሞች በአንዱ አጎራባች ላይ የሚኖሩ አንድ ኢትዮጵያዊ፣ ልክ የዛሬ ሳምንት ማክሰኞ ምሽት ላይ ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ የአደጋ ጥሪ ሲደረግላቸው እሳቱን ከርቀት ይመለከቱት እንደነበር ተናግረዋል።

እሳቱ በተዛመተበት ደቡባዊ ክፍል በምትገኘው ሳንታ ሞኒካ ከተማ ነዋሪ የኾኑት የእንስሳት ሃኪሙ ዶ.ር በርገኔ ባንጫ ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ከተነገራቸው ነዋሪዎች አንዱ ነበሩ። በዕለቱ ያጋጠማቸውን አጋርተውናል። ቃለ ምልልሱን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG