በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪ ወላጆች አቤቱታ


 በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪ ወላጆች አቤቱታ
በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪ ወላጆች አቤቱታ

በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ልጆቻችንን ከክልሉ ለማስወጣት “የገባውን ቃል አላከበረም” በማለት በአዲስ አበባ የሚገኙ የተማሪ ወላጆች የተባበሩት መንግሥታትን ወቀሱ።

አዲስ አበባ የሚገኙ በርካታ ቁጥር ያላቸው የተማሪ ወላጆች እና ሌሎች የቤተሰብ አባላት በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ደጅ ላይ ተሰባስበው፣ “በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ልጆቻችንን በአስቸኳይ መልሱልን” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ድርጅቱ በትግራይ ክልል ባሉ የዩኒቨርሲቲዎች እና በኢትዮጵያ ሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መካከል በመሆን፣ ተማሪዎችን የማስመለሱን ኃላፊነት ለመወጣት ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የጠየቀው የነዳጅ እና ሌሎች አቅርቦቶች ጥያቄዎቹ እንደተመለሱለት ማረጋገጣቸውን የሚገልጹት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ ሆኖም ድርጅቱ ኃላፊነቱን እንዳልተወጣ ተናግረዋል፡፡

በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪ ወላጆች አቤቱታ
በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪ ወላጆች አቤቱታ

የወላጆች ተወካይ ኮሚቴ አባል መሆናቸውን የሚገልጹት አቶ ዳንኤል አስራት ተመድ በስተመጨረሻ ተማሪዎችን መያዣ በማድረግ ከስምምነት ውጭ የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎችን መንግሥት እንዲፈጽም ስለማስቀመጡ ተናግረው አሁን ላይ በድርጅቱ ተስፋ እንደሌላቸው ስሜታቸውን ገልጸዋል፡፡

በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ኩያ ካምፓስ የአምስተኛ ኛ ዓመት ተመራቂ ልጅ እንዳለቻቸው የሚናገሩት ወ/ሮ ኢየሩሳሌም ታፈሰ፣ የተማጽኖ ድምጻቸውን ለማሰማት ከተሰባሰቡ ሰዎች አንዷ ናቸው፡፡

የተባበሩት መንግሥታት፣ በትግራይ ክልል ባሉ የዩኒቨርሲቲዎች እና በኢትዮጵያ ሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መካከል በመሆን፣ ከሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በክልሉ የሚገኙ ተማሪዎችን የማስመለሱን ኃላፊነት ለመወጣት ቃል ገብቶ እንደነበር የተማሪ ወላጆች እና ሌሎች ቤተሰቦቻቸው ይናገራሉ፡፡

ከተማሪ ወላጆች መካከል የሆኑት ወ/ሮ ፍሬሕይወት ገብረሕይወት እና አቶ ቢንያም አስራት የተባበሩት መንግስታት ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል የጠየቀው የነዳጅ እና ሌሎች አቅርቦቶች ጥያቄዎች እንደተመለሱለት ማረጋገጣቸውን ገልጸው፣ ይሁንና ድርጅቱ ኃላፊነቱን አልተወጣም ብለዋል፡፡

የዛሬውን ጨምሮ ለሦስት ጊዜያት የተባበሩት መንግሥታትን ደጅ ከመጥናት ጀምሮ መፍትሔ ፍለጋ ወደ ተለያዩ አካላት ቢሔዱም ከተስፋ ውጭ ተጨባጭ ውጤት እንዳላገኙ የሚገልጹት እና በመቀሌ አይደር ካምፓስ ሁለት ሴት ልጆች አሉኝ ያሉት ወ/ሮ ገነት ሮባ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

የወላጆች ተወካይ ኮሚቴ አባል በመሆን በአዲስ አበባ ከተባበሩት መንግስታት ኃላፊዎች ጋር ተማሪዎቹን ማስወጣት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ሲነጋገሩ መቆየታቸውን የሚገልጹት አቶ ዳንኤል አስራት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በስተመጨረሻ ተማሪዎችን መያዣ በማድረግ ከስምምነት ውጭ የሆኑ ቅድመ ሁነኔታዎችን መንግሥት እንዲፈጽም ስለማስቀመጡ ያነሳሉ፡፡ እናም አሁን ላይ በድርጅቱ ተስፋ እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

ምንም እንኳን ከተማሪዎቹ ጋር ባይገናኝም፣ ተመድን ጨምሮ የተለያዩ አካላት፣ ለሰብዓዊ አገልግሎቶች ተደራሽነት ይረዳ ዘንድ የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል እንደ መብራትና ስልክ ያሉ አገልግሎቶችን በተሟላ መልኩ እንዲያቀርብ በተደጋጋሚ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡

የተማሪ ወላጆች በተመድ ላይ ስላቀረቡት ወቀሳ ምላሽ ለማግኘት እንዲሁም በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ከክልሉ ውጭ የሄዱ ተማሪዎችን ለማስወጣት ድርጅቱ ስለሄደበት ርቀት ለመጠየቅ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የድርጅቱን ሰራተኞች እና ኃላፊዎች ለማግኘት ቪኦኤ በተለያየ መልኩ ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ የሳይንስ እና ከፍተኛ ሚኒስቴርንም እንዲሁ ለማግኘት ጥረት ብናደርግም ሊሳካልን አልቻለም፡፡ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሚኒስቴሩ በዚሁ ጉዳይ ላይ የሰጠው ምላሽም የለም፡፡

በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪ ወላጆች አቤቱታ
በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪ ወላጆች አቤቱታ

በተለያየ ቀውስ ውስጥ በሚገኘው የትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ስላሉ ተማሪዎቻቸው ጉዳይ መረጃን ለማግኘት በፍለጋ ላይ ያሉ ወላጆቻቸው፣ እስካሁን ለልጆቻችን ድጋፍ እና ጥበቃ አድርገዋል ያሉትን የትግራይ ክልልን ሕዝብ አመስግነው፣ ይህ ተግባር እንዲቀጥልም ተማጽኖአቸውን አቅርበዋል፡፡

በሌላ በኩል መቀሌ ዩኒቨርስቲ ከሃምሌ 20/2013 ዓ.ም ጀምሮ በተማሪዎች ላይ ለሚከሰተው የምግብ እጦት ኃላፊነት አልወስድም አለ። ዩኒቨርስቲው የሰኔ ወር በጀት እንዳልተላከለት እና በባንክ ያለውን ገንዘብ ለማንቀሳቀስ እንደተቸገረ ገልጿል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪ ወላጆች አቤቱታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:31 0:00


XS
SM
MD
LG